Back to Exhibitions & Events
ExhibitionOngoing

የሚጨሰው ጠረጴዛ

በፕሮፌሰር Bekele Mekonnen የተዘጋጀው “የሚጨሰው ጠረጴዛ” የኢንስታሌሽን ሥነ ጥበብ ቋሚ ዓውደ ትርዒት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለዕይታ በቅቷል።

Participating Artists

Bekele Mekonnen

September 19, 2026Adwa Victory Memorial Museum, Addis Ababa
የሚጨሰው ጠረጴዛ

About the exhibition

ይህ ጉልበታም የሥነ ጥበብ ሥራ የዓለምን ታሪክ በጉልህ የቀየረውን የዓድዋ ድል እንደ ድል አድራጊ በወጉ፣ “በአሸናፊ ዐይን” እንድናየው ይጋብዘናል። ከቱርፉቱ ልብ በሚያሞቅ መልኩም ይህን ታሪክ በአገር ግንባታም ሆነ በሥነ ልቦና ዘርፍ እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል ከልብ እንድንጠይቅ የሚያደርገን ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

በዕይታዊ ጥበብ፣ በተለያዩ ጊዜያት የዓድዋን ድል ለመዘከር ከተሠሩ ሥራዎች በተለየ አቀራረቡና ኪነ ጥበባዊ ትርጓሜው፣ በሙዚቃው ዘርፍ ስለ ዓድዋ ድል ከተዜመው ከእጅጋየሁ ሽባባው “ዓድዋ” ዜማ እኩል፣ በዐይን ገብቶ በልብ የሚዜም ሥራ እንደሆነ አይቻለሁ።

ሥራው ካፒታሊስት መንግሥታት በኃይል የወረሯቸውን ሀገሮች ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ነፃነት የገፈፉበትንና በተገዢነት ቀንበር ሥር እንዲውሉ የተጠቀሙበትን ሥርዓትና ፖሊሲ የተመካከሩበትን የበርሊን ኮንፈረንስ ጠረጴዛን እንደ መነሻ ያደረገ ነው።

በ120 ሳ.ሜ. × 480 ሳ.ሜ. × 220 ሳ.ሜ. መጠን የተዋቀረው ይህ የፈጠራ ሥራ፣ ጉዳዩ ከተፈፀመበት ቦታና ጊዜ ቢርቅም፣ ዛሬ ድረስ ብዙ የሚያነጋግሩን ጉዳዮችን ያነሳል። ከእነዚህ ውይይቶች የሚወለዱት ሐሳቦችም የነገ ብሩህ ተስፋችንን እንደሚያመላክቱ አምናለሁ።

Kirubel Melee